ዲሞክራሲን ለማራመድ፣ ሁሉም ድምፆች እንዲሰሙና  እና መብቶች እንዲከበሩ ብዝሃ-ተኮር የሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፍን እንገንባ!

የሲቪል ሶሳይቲ ኢኖቬሽን ፈንድ (CSIF) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠሩ 15 አዳዲስ እና ጀማሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ይደግፋል። ፕሮግራሙ በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ (AFD) የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ነው። CSIF ከግንቦት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል

ብዝሃ-ተኮር የሲቪል ማኅበረሰብ ምህዳር በኢትዮጵያ

የሲ ኤስ አይ ኤፍ (CSIF) ኢትዮጵያ ዓላማ የሲቪል ማኅበረሰብ ብዝሃነትን እና ፈጠራን ማጠናከር፣ ብዝሃ-ተኮር እና ዲሞክራሲያዊ የሲቪል አደረጃጀቶችንና የዜጎችን የነቃ ተሳትፎ በማረጋገጥ የዜጎች እና የማኅበራትን የመደራጀት መብቶች እንዲከብሩ ማድረግ ነው፡፡

 ሲ ኤስ አይ ኤፍ (CSIF) ኢትዮጵያ በ15 የሲቪል ማኅበራት ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉትን ፕሮጀክቶችን ከመደገፍ ባሻገር የድርጅቶቹን አቅም የሚያጎለብቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሲ ኤስ አይ ኤፍ (CSIF) ፕሮጀክቶች

የፈንዱን ዓላማ ለማሳካት ሶስት ፕሮጀክቶች በጥንቃቄ የተመረጡ ሲሆኑ እያንዳንዱ ፕሮጀክት የሚተገበረው አዲስ እና ጀማሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በሚያሳትፍ ጥምረት ነው።

1ኛ ፕሮጀክት

የሰብዓዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ ጥናት፣ ምክክርና ሙግት በማካሄድ አካታች ማኅበረሰብን መገንባት

2ኛ ፕሮጀክት

ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት የሰብዓዊ መብት አያያዝን ማሻሻል

3ኛ ፕሮጀክት

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ተሳትፎ ፕሮግራም 

የሲ ኤስ ኤፍ ኢትዮጵያ አስተዳደርና ማስተባበሪያ

በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ እና አጋር (AGAR)በኢትዮጵያ እና በ INTRAC UK የሚተዳደር

የገንዘብ ድጋፍ

በቴክኒካዊ ድጋፍ